
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን በዱር ቤቴ ከተማ አሥተዳደር “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሰልፈኞቹ መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደሚደግፉ እና ለዚህም እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።
የሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፈኞች የጽንፈኛው ኀይል በንፁሀን ላይ የሚፈጽመውን ግድያ፣ ማንገላታት እና ማፈናቀል ሊያቆም ይገባል ነው ያሉት።
ሰላም የጋራ ሃብት እንደኾነም አስገንዝበዋል።
ሕጻናትን ከትምህርት ገበታቸው ማስቀረት የጽንፈኝነት ጥግ ነው ያሉት ሰልፈኞቹ ልጆቻቸው ያለችግር እንዲማሩ እንደሚፈልጉም ነው የተናገሩት።
የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች በውይይት እንጅ በጦርነት የሚፈቱ አይደሉም ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!