
ደብረ ብርሃን: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር “ለሰላም ዘብ እንቁም”በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በሰልፉ ላይ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
ሰልፈኞቹ በመፈክሮቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስደውን ርምጃ እንደሚደግፉ ተናግረዋል።
ሰላም የጋራ ሃብት ነው ያሉት ሰልፈኞቹ በጋራ እንደሚያለሙት እና በጋራ እንደሚጠብቁትም አስረድተዋል።
መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን ርምጃዎች እንደሚደግፉም ነው ያብራሩት።
ሰልፈኞቹ ለክልሉ የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ሰላም እንደኾነ ነው የተናገሩት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!