በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር መንግሥት በተደጋጋሚ ያቀረበውን የሰላም ጥሪ የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

21

ደሴ: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰልፉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድአሚን የሱፍ “የአማራ ሕዝብ ጥያቄ የሚመለሰው በሕዝባዊ አንድነት እና በኅብረ ብሔራዊነት እሳቤ እንጅ በነፍጥ የሚፈታ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ አለመኖሩን በመረዳት የሰላምን አማራጭ ተቀብለን ወደ ልማት መመለስ አለብን ብለዋል”

ሰልፈኞቹ በመልዕክቶቻቸው፦
👉 ”መንግሥት በተደጋጋሚ ያቀረበውን የሰላም አማራጭ እንደግፋለን”
👉 ”ጦርነት ይብቃን ሰላም ይስፈን”
👉 ”ሰላም የጋራ ሃብታችን ነው”
👉 ”መንግሥት ሕግ ለማስከበር እየወሰደ ያለውን ርምጃ እንደግፋለን” የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን በማንገብ በሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሰልፉ ላይ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተማሪዎች፣ የመንግሥት ሰራተኞች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የኮምቦልቻ ከተማ ማኅበረሰብ ተሳታፊ ኾነዋል።

ዘጋቢ:- ደምስ አረጋ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጽንፈኛ ቡድኑ የሚያደርሰውን ግፍ እና በደል እንደሚቃወሙ የሞጣ ከተማ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ።
Next article“ዛሬ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝብ ሰላምን የፈለገበት፣ ጦርነትን ያወገዘበት ነው” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው