
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ በክልሉ ሕግን ለማስከበር የሚሠራውን ሥራ የሚደግፍ እና ጽንፈኛው ቡድን የሚያደርሰውን ግፍ እና በደል የሚቃወም ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደሚደግፉ ተናግረዋል።
ክልሉን የሰላም እና የልማት ማዕከል ለማድረግ ለሰላም ዘብ እንደሚቆሙ የተናገሩት ነዋሪዎቹ መንግሥት ሕግ በማስከበር የንፁሃን ሰዎችን ሕይዎት እንዲታደግ ነው የጠየቁት።
መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን ርምጃዎች እንደሚደግፉም ባሰሙት መፈክር አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!