
ባሕር ዳር: ታኅሳስ 9/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በባቲ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በሰልፉ ላይ ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተማሪዎች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳታፊ ኾነዋል።
የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች የሰላምን ዋጋ ለማወቅ የግድ ሰላም ማጣት የለብንም፤ ሰላም በገንዘብ የማይተመን ውዱ እና አስፈላጊው የሕይዎት ገጽታ ነው በማለት የተለያዩ መልዕክቶችን እያሰሙ ወደ ኳስ ሜዳ አደባባይ እየሄዱ ይገኛሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!