
ደባርቅ: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ለሰላም ዘብ እንቁም” በሚል መሪ መልዕክት በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። ነዋሪዎቹ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እንዳሉት፦
✍️ መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን።
✍️ ክልላችንን የሰላም እና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን።
✍️ መንግሥት ሕግ በማስከበር የንፁሃን ሰዎችን ገዳዮች ለሕግ ያቅርብልን።
✍️ መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን ርምጃዎች እንደግፋለን።
✍️ በደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት ከተማ ጽንፈኛው ኀይል በንፁሀን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ እና ግድያ በጽኑ እናወግዛለን።
✍️ ንፁሀንን በግፍ እየገደሉ በአስከሬናቸው መነገድ አረመኔያዊነት ነው።
✍️ የልማት ማዕከል የነበረውን ክልላችንን የጦርነት ቀጣና ለማድረግ የሚሠራው ሥራ የባንዳነት እና የጽንፈኝነት ጥግ ነው።
✍️ ንፁሀንን በግፍ መጨፍጨፍ የአረመኔነት ጥግ ስለኾነ ሊወገዝ ይገባዋል።
✍️ ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ሰላም እና ልማት ነው።
✍️ ጽንፈኛ እና ተላላኪዎች ከባዕዳን ተልዕኮ ወጥተው የሰላምን አማራጭ ሊከተሉ ይገባል።
✍️ ሰላም የጋራ ሃብት ነው፤ በጋራ ይለማል በጋራ ይጠበቃል።
✍️ መንግሥት ሕግ በማስከበር የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ሊያስጠብቅ ይገባል።
✍️ ጽንፈኛው ኀይል በንፁሃን ላይ የሚፈጽመው ግድያ፣ ማገት እና ማፈናቀል ሊቆም ይገባል።
✍️ መከላከያ ሠራዊታችን፣ የፌዴራል የጸጥታ ኀይሎች እና የክልላችን የጸጥታ ኀይሎች ለከፈሉት ዋጋ ክብር እንሰጣለን የሚሉ መልዕክቶችን ነዋሪዎቹ አሰምተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!