
ሀርቡ: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን በሀርቡ ከተማ አሥተዳደር ጽንፈኞችን የሚያወግዝ የሕግ ማስከበሩን የሚደገፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነዉ።
በሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በሰልፈኞች የተለያዩ መልዕክቶች እየተላለፈ ሲሆን መልዕክቶቹም፦
👉 መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን!
👉 በደምበጫ በገርጨጭ፣ በላሊበላና በሌሎች አካባቢዎች ንፁሃንን የጨፈጨፉ ፅንፈኛ ኀይሎች ለሕግ ይቅረቡልን!
👉 ክልላችንን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን!
👉 መንግሥት ሕግ በማስከበር የንፁሃን ሰዎችን ገዳዮች ለሕግ ያቅርብልን!
👉 መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን!
👉 በደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት ከተማ ፅንፈኛው ኀይል በንፁኀን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋና ግድያ በፅኑ እናወግዛለን!
👉 ንፁኀንን በግፍ እየገደሉ በአስከሬናቸው መነገድ አረመኔያዊነት ነው!
👉 የልማት ማዕከል የነበረውን ክልላችንን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ የሚሠራው ሥራ የባንዳነትና የፅንፈኝነት ጥግ ነው!
👉 ንፁኀንን በግፍ መጨፍጨፍ የአረመኔነት ጥግ ስለሆነ ሊወገዝ ይገባዋል!
👉 ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰላም እና ልማት ነው!
👉 ፅንፈኛ እና ተላላኪዎች ከባዕዳን ተልዕኮ ወጥተው የሰላምን አማራጭ ሊከተሉ ይገባል!
👉 ሰላም የጋራ ሀብት ነው፤ በጋራ ይለማል በጋራ ይጠበቃል!
👉 መንግሥት ሕግ በማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል!
👉 ፅንፈኛው ኀይል በንፁሃን ላይ የሚፈፅመው ግድያ፣ ማገትና ማፈናቀል ሊቆም ይገባል!
👉 መከላከያ ሠራዊታችን፣ የፌዴራል የፀጥታ ኀይሎች እና የክልላችን የፀጥታ ኀይሎ ለከፈሉት ዋጋ ክብር እንሰጣለን!
በአንተነህ ጸጋየ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!