
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ሕዝባዊ ሰልፍ ላይም የተማሪዎች ድምጽ ከፍ ብሎ ተሰምቷል።
የሰላም መጥፋት ከብዙ ምስቅልቅሎች በተጨማሪ የልጆችን የመማር መብት አሳጥቷል።
በተለይም በአማራ ክልል በርካታ ተማሪዎች የሚናፍቋቸው የዕውቀት በሮቻቸው ተዘግተውባቸው ከርመዋል። ይህም መሥከረም ጠብቶ ዕውቀታቸውን ማስቀጠል የናፈቁ ተማሪዎችን ቅስም ሰብሯል።
“ደብተር እና ብዕር እንጅ ጥይት አንፈልግም፤ ታጣቂዎች እጃችሁን ከትምህርት ቤታችን እና ከህልማችን ላይ አንሱ” በማለት በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ ታድመዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!