
ጎንደር: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰልፉ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ሲኾን ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚጠይቁ መፈክሮች እየተሰሙ ነው።
👉 ክልላችን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ለሰላም ዘብ እንቆማለን!
👉 መንግሥት የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ያስጠብቅ!
👉 መንግሥት ሰላምን ለማስከበር የሚወስዳቸውን ርምጃዎች እንደግፋለን!
👉 ህፃናት የጽንፈኛ ኀይሎች መነገጃ አይደሉም!
👉 መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን!
👉 እኛ ተማሪዎች በሰላም መማር እንፈልጋለን!
👉 ለከተማችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ንፁህ መጠጥ ውኃ ነው!
👉 ሰላም የጋራ ሃብት ነው በጋራ ይጠበቃል።
👉 እንዲሁም የፌዴራል መንግሥት ለጎንደር ከተማ እያደረገ ላለው ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያመሰግኑ መፈክሮች እየተሰሙ ነው።
የሰልፍ ሥነ ሥርዓቱ በፋሲለደስ ስታዲየም መዳረሻውን አድርጎ የተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከወኑ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!