በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር እንዲቆም እና ሰላም እንዲሰፍን የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ።

73

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

ሰላማዊ ሰልፉ በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር እንዲቆም እና ሰላም እንዲሰፍን የሚጠይቅ ነው።

በሰላማዊ ሰልፉ:-

👉 ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ሰላም እና ልማት ነው።

👉 መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን ርምጃዎች እንደግፋለን።

👉 መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን።

👉 መንግሥት ሕግ በማስከበር የንጹሐን ሰዎችን ገዳዮች ለሕግ ያቅርብልን።

👉 ሰላም የጋራ ሃብት ነው፣ በጋራ ይለማል፣ በጋራ ይጠበቃል።

👉ክልላችንን የሰላም እና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን።

👉ጽንፈኛው ኀይል በንጹሐን ላይ የሚፈጽመው ግድያ፣ ማገት እና ማፈናቀል ሊቆም ይገባል።

👉ጽንፈኞች እና ተላላኪዎች ከባዕዳን ተልዕኮ ወጥተው የሰላምን አማራጭ ሊከተሉ ይገባል።

👉ንጹሐንን በግፍ እየገደሉ በአስከሬናቸው መነገድ አረመኔያዊነት ነው የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን እያሰሙ ነው።

በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ኾነዋል።

የክልሉ ሕዝብ መደበኛ የማኅበራዊ እንቅስቃሴ ተጎድቷል። መጠነ ሰፊ ጉዳትም ደርሷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበእንጅባራ ከተማ መንግሥት እየወሰደ ያለው ሕግ የማስከበር ርምጃ የሚደግፍ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next article“ለሰላም ዘብ እንቆማለን” በሚል መሪ መልእክት በጎንደር ከተማ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።