
እንጅባራ: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በድጋፍ ሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሰራተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አዛውንቶች፣ ተማሪዎች እና ሌሎችም የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ሰልፈኞቹ ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ሰላም እና ልማት ነው፣ የመንግሥት ሕግ የማስከበር ርምጃን እንደግፋለን፣ መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያቀርበውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን የሚሉ እና ሌሎችንም መልዕክቶች እያስተጋቡ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!