
ደሴ: ታኅሳስ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች የተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
የተለያዩ መልእክቶችን የያዙት ሰላማዊ ሰልፈኞች “ጦርነት ይብቃ ሰላም ይስፈን” በማለት ወደ ሆጤ ስታዲዬም እየተጓዙ ነው።
በሰላማዊ ሰልፉ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ የመንግሥት ሰራተኞች እና የከተማው ሕዝብ እየተሳተፈ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!