“ለሰላም ዘብ እንቁም” የሚል መልእክት የያዘው የባሕር ዳር ከተማ ሕዝባዊ ሰልፍ ተጀምሯል።

76

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ የተገኘውን ሰላም የሚደግፍ፣ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ደግሞ የሚጠይቅ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው። እንደ ክልል ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀው የሰላም እጦት የክልሉን ነዋሪዎች ሲፈትን ቆይቷል።

የሕዝቡ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎችም እንቅስቃሴዎች ተገድበው ቆይተዋል። ክቡር የኾነው የሰው ሕይዎት ጠፍቷል፤ መሠረተ ልማቶች ወድመዋል። በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው አቋርጠው የተወዳዳሪነት ጉዟቸው ተሰናክሏል።

የሰላም እጦት ችግሩ የኑሮ ውድነትን አባብሷል፤ ሥራ አጥነትን ወልዷል። ሰርተው የሚያድሩ እጆች ታጥፈዋል፤ ነግደው የሚያተርፉ ንግዳቸውን ዘግተዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የክልሉ የጸጥታ ተቋማት ባደረጉት ሕግ የማስከበር ተግባር የክልሉ ሰላም ተመልሷል። በዚህ የተደሰቱ ነዋሪዎችም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተገኘውን ሰላም በመደገፍ፣ በቀጣይም አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን በመጠየቅ ሕዝባዊ ሰልፎችን እያካሄዱ ነው።

በባሕር ዳር ከተማም በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች “ለሰላም ዘብ እንቁም” በሚል መሪ መልእክት ሕዝባዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመንግሥት እየሠራ ያለውን ሰላም የማስከበር ተግባር የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ በኮምቦልቻ ከተማ እና አካባቢው እየተካሄደ ነው።
Next articleበደብረ ማርቆስ ከተማ ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።