
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ እና አካባቢው ነዋሪዎች “ጦርነት ይብቃ ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ መልዕክት ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከያዟቸው መልዕክቶች መካከል፦
👉መንግሥት ሰላም ለማስከበር የሚሠራውን ሥራ እንደግፋለን
👉ሀገራችን የሚያስፈልጋት ጦርነት ሳይኾን ሰላም ነው
👉መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን
👉ለክልላችን ሰላም ዘብ እንቆማለን
👉 የንጹሀን ግድያ ይቁም የሚሉ ይገኙበታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!