መንግሥት እየሠራ ያለውን ሰላም የማስከበር ተግባር የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በአዴት ከተማ እየተካሄደ ነው።

61

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዴት ከተማ መንግሥት እየሠራ ያለውን ሰላም የማስከበር ተግባር እንደሚደግፉ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ገልጸዋል።

በሰሜን ጎጃም ዞን አዴት ከተማ “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት አደባባይ የወጡት ነዋሪዎቹ የተለያዩ መልዕክቶችን አሰምተዋል።

ነዋሪዎች ባሰሙት መልዕክት መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደሚደግፉ ነው የገለጹት።

ተማሪዎች በሰላም እንዲማሩ፣ ሕዝቡ በሰላም ወጥቶ እና ሠርቶ እንዲገባ፣ ከክልሉ የወጡ ባለሃብቶች እንዲመለሱ መንግሥት የጀመረውን ሰላም የማረጋገጥ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሰቆጣ ከተማ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next articleመንግሥት እየሠራ ያለውን ሰላም የማስከበር ተግባር የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ በኮምቦልቻ ከተማ እና አካባቢው እየተካሄደ ነው።