
ሰቆጣ: ታኅሳስ 9/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላማችን በማጽናት ልማታችን እናስቀጥላለን” በሚል መሪ መልዕክት በሰቆጣ ከተማ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየካሄደ ነው።
ሰላማችን በማጸናት ልማታችንን እናስቀጥላለን በሚል መሪ መልዕክት በሰቆጣ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ አየተካሄደ ነው።
ሰልፈኞቹም “ልማታችን በእጃችን ነው፣ ልማታችንን ለማምጣት ሰላማችንን ልንጠብቅ ይገባል፣ ለአማራ ክልል ልማት እንጂ ጦርነት አይገባውም፣ መከላከያ ሰራዊታችንን እንደግፋለን፣ ጽንፈኛ ኃይሎችን እንቃወማለን” የሚሉ መልዕክቶች በሰልፈኞቹ እየተንጸባረቁ ነው።
በሰለማዊ ሰልፉም የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት ሰራተኞች እና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!