በገንዳ ውኃ ከተማ መንግሥት የሕዝብን ሰላም ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

63

ገንዳ ውኃ: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት በገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ “ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ሰላም እና ልማት ነው” በሚል መሪ መልዕክት ነው ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ያለው።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ “ሰላም እንፈልጋለን፣ ጽንፈኝነት በቃ፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ያለምንም ስጋት ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሱ፣ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን፣ የመንግሥትን የሕግ የበላይነት ማስከበር እንደግፋለን፣ መንግሥት የዜጎችን ወጥቶ መግባት፣ ተንቀሳቅሶ ሃብት የማፍራት መብትን ያስከብርልን” የሚሉ መልዕክቶችን እያሰሙ ነው።

በድጋፍ ሰልፉ ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የዞን እና የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች፣ የተለያዩ የሥራ ማኅበራት፣ መምህራን እና ተማሪዎች፣ የግል ድርጅቶች እና የከተማ አሥተዳደሩ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ የጋራ የሚኒስትሮች ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
Next articleበሰቆጣ ከተማ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።