
አዲሰ አበባ: ታኅሣሥ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጉባኤው ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ሲኾን የሁለቱን ሀገራት የልማት ትብብር የሚያሳድግ ነው።
የኢትዮጵያ እና የታንዛኒያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ እና በሁለቱም በኩል በርካታ የሀገራቱ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል። ይህ ለሀገራቱ ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ተብሏል።
የጋራ የሚኒስትሮች ጉባኤ የሚመሩት የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሲኾኑ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነድ ይፈራረማሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!