ኢጋድ ድንበር ተሻጋሪ ስጋቶችን መከላከል ታሳቢ ያደረገ ሕገ-ደንብ ሊያጸድቅ ነው።

26

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ድንበር ተሻጋሪ ስጋቶችን መከላከል ዓላማ ያደረገ ሕገ-ደንብ አጽድቆ ወደ ትግበራ ሊያስገባ መኾኑ ተገልጿል።

በሕገ ደንቡ የመጨረሻ ረቂቅ ላይ የሚመክር የኢጋድ ከፍተኛ ቀጣናዊ ፎረም ዛሬ በኬንያ ሞምባሳ መካሄድ ጀምሯል።

የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር እና የኢጋድ የአምባሳደሮች ኮሚቴ ሠብሣቢ መሐመድ ዓሊ ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ሥብሠባን አስጀምረዋል።

ፎረሙ ድንበር ተሻጋሪ ስጋቶችን መከላከል እና መቆጣጠር በሚያስችለው ረቂቅ ሕገ-ደንብ ላይ በመምከር እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።

የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ.ር) ሕገ ደንቡ ጸድቆ ወደ ሥራ ይገባል የሚል ዕምነት እንዳላቸው በኤክስ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የኢጋድ አባል ሀገራትን የሚወክለው እና የፖሊሲ ውሳኔ ሰጭ አካል የኾነው የኢጋድ የአምባሳደሮች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ኮሚቴ የጋራ ጸጥታን ለማጠናከር በቅንጅት መሥራት አስፈላጊ መኾኑን አስገንዝቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አሚኮ የሕዝብን አንድነት በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው” ጃንጥራር ዓባይ
Next articleየኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ የጋራ የሚኒስትሮች ጉባኤ እየተካሄደ ነው።