የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ያሰለጠናቸውን ሚሊሻዎች አስመረቀ።

53

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 8/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ያሰለጠናቸውን ሚሊሻዎች አስመርቋል።

ከተማ አሥተዳድሩ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲሰጣቸው የቆዩ የሚሊሻ አባላትን ነው ያስመረቀው።

ከደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ኮምዩንኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ተመራቂዎቹ በከተማዋ ያለውን አሁናዊ ሰላም በዘላቂነት በማጽናት ከተማ አሥተዳደሩ በሙሉ አቅሙ ልማት ላይ እንዲያተኩር ለማስቻል ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው ተመላክቷል።

በአማራ ክልል የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ወደ ዘላቂ ሰላም ለመመለስ በተለያዩ አካባቢዎች ሚሊሻዎች እየለጠኑ ወደ ሰላም ማስከበር ሥራው እየገቡ ነው። ሚሊሻዎች እየሰለጠኑ ወደ ሥራ መግባታቸው ክልሉን ወደ ዘላቂ ሰላም ለመመለስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየውጭ ባንኮች በሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ የሚያስችል አዋጅ ጸደቀ።
Next article“አሚኮ የሕዝብን አንድነት በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው” ጃንጥራር ዓባይ