
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል። አዋጁ የውጭ ባንኮች በሀር ውስጥ ገብተው መሥራት እንዲችሉ የሚያደርግ መኾኑ በምክር ቤቱ ተነስቷል።
አዋጁን በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎች ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ እስመለዓለም የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው የባንኩን ዘርፍ የሚያነቃቃ እና የባንክ ኢንቨስትመንትን የሚያሳድግ ነው ብለዋል።
አዋጁ የውጭ ባንኮችን ብቻ መሠረት ያደረገ ሳይኾን የሀገር ውስጥ ባንኮችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች የተቀመጡበት እንደኾነም አብራርተዋል።
ባንኮቹ ወደ ኪራሳ እንዳይገቡ የሚያስችል መውጫ መንገዶችን የሚጠቁም መኾኑንም ነው የገለጹት ።
ይህ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅም በምክር ቤቱ አብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉዑሽ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!