
ደብረ ብርሃን: ታኅሣሥ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰላም እጦት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ለከፋ ችግር እንዳይጋለጡ የበኩሉን እየተወጣ መኾኑን ፋብሪካው አስታውቋል።
475 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት ድጋፍ መደረጉን በፋብሪካው የማኅበራዊ አገልግሎት ጉዳይ ኀላፊ ጌታነህ ዝቄ ተናግረዋል።
በተፈናቃዮች ጊዜያዊ መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችም የሰላም ሁኔታው ቢስተካከል ወደ ቀደመ ቀያቸው የመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው አስረድተዋል። ለተደረገላቸው ድጋፍም አመስግነዋል።
መንግሥት ዘላቂ መፍትሄ በማመቻቸት ከችግር እንዲያላቅቃቸውም ጠይቀዋል።
ዘጋቢ:- አበበች የኋላሸት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!