
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም “በሚል መሪ ሀሳብ ከከተማዋ ወጣቶች ጋር በሰላም እና በልማት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄዷል።
በመድረኩ በመከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል ኀላፊ ሜጀር ጀኔራል አዳምነህ መንግሥቴ፣ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ መኳንት አደመ፣ የአማራ ክልል ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት አማካሪ ይትባረክ አወቀ፣ የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እድሜዓለም አንተነህ፣ የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ማማሩ ሽመልስ እና ሌሎች የዞን እና የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!