
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሚያ ክልል ለሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሠባሠብ ሥራ እየተካሄደ ነው። በአጀንዳ የማሠባሠብ ሥራ መድረክ ላይ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች እየተሳተፉ ነው የሚገኙት።
ዛሬ እየተካሄደ ባለው የአጀንዳ ማሠባሠብ ሥራ ላይ ከ356 ወረዳዎች የተውጣጡ ከ7ሺህ በላይ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች እየተሳተፉ ነው። የመድረኩ ተሳታፊዎች የመወያያ አጀንዳዎችን በመለየት ላይ እንደሚገኙም ለአሚኮ ተናግረዋል።
የኅብረተሰቡን ጥያቄዎች በማሠባሠብ በሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ ላይ በማቅረብ ሕዝቡ የሰጣቸውን አደራ ለመወጣት እየሠሩ እንደሚገኙም የኅብረተሰቡ ተወካዮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!