የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የመሠረቱት ፋውንዴሽን ይፋ ሆነ።

45

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የመሠረቱት “የአዳም ፋውንዴሽን” የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ምሥረታውን ይፋ አድርጓል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመሩት “የአዳም ፋውንዴሽን” የመንግሥት ባለስልጣናት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት በተገኙበት ይፋዊ የማብሰሪያ ሥነ ሥርዓቱን በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ልማትና እድገት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የገለፁት የፋውንዴሽኑ መስራች አቶ ደመቀ መኮንን፤ በተለይ ህፃናትና እናቶች ላይ በመስራት ብሎም መቀንጨርን በመዋጋት ደህንነቱ የተጠበቀ ትውልድ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሠሩ ገልፀዋል።

“በአፍሪካ መቀንጨርን መግታት” የሚል መሪ ሀሳብ ያለው ፋውንዴሽኑ፤ ከኢትዮጵያ የሲቪል ማበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘው ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ እንደነበር ተገልጿል።

ኢቢሲ እንደዘገበው “የአዳም ፋውንዴሽን” በሥነ ምግብ ላይ መሥራት ዋና ዓላማው ያደረገ ሲሆን መቀንጨርን ለመግታት የሚያስችሉ ባለብዙ ዘርፍ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ይሠራል ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየእስራኤል ባለሃብቶች በአማራ ክልል ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ተናገሩ።
Next articleየትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ.ር) በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አሥተዳደር የበጋ ስንዴ ዘር አስጀመሩ።