በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል የተሳታፊ እና የአጀንዳ ልየታ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።

34

አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኮሚሽኑ ይህን ያለው የሀገራዊ የምክክር አጀንዳዎች የማሰባሰብ ሥራ በአዳማ ከተማ በተጀመረበት መድረክ ላይ ነው።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መሥፍን አርኣያ በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት የዘገየውን የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የተሳታፊዎች ልየታ በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ኮሚሽኑ በእስካሁን ቆይታው በ9 ክልሎች እና ሁለት ከተማ አሥተዳደሮች የአጀንዳ ልየታ ሥራ ማከናወኑን ተናግረዋል። በ971 የኢትዮጵያ ወረዳዎች የተሳታፊዎች ልየታ መከናወኑንም ዋና ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

ዘጋቢ:- ሽመልስ ዳኜ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለ25ኛው የአፍሪካ ኢቫሉዌሽን አሶሴሽን የዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next articleየወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማሽን በድጋፍ አገኘ።