
አዲስ አበባ:- ታኅሣሥ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በመጪዉ ሰኔ ኢትዮጵያ ለምታዘጋጀው 25ኛው የአፍሪካ ኢቫሉዌሽን አሶሴሽን መርሐ ግብር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኢቫሉዌሽን አሶሴሽን እና ከአፍሪካ ኢቫሉዌሽን አሶሴሽን ጋር በመርሐ ግብሩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።
በውይይቱም ኢትዮጵያ ሰኔ ላይ ለምታዘጋጀው ለዚህ አህጉራዊ ፕሮግራም ከአጋር አካላት ጋር የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገች እንደምትገኝ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሃፅዮን ተናግረዋል። ይህን መድረክ ኢትዮጵያ ማዘጋጀቷ ትልቅ አቅም ይፈጥርላታል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ኢቫሉዌሽን አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ደረጀ ማሞ ናቸው።
የአፍሪካ ኢቫሉዌሽን አሶሴሽን ፕሬዝዳንት ሚሼ ኦውድራጎ (ዶ.ር) ፕሮግራሙ የተሳካ እንዲኾን የኢትዮጵያ መንግሥት እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ቤቴል መኮንን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!