
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ ) ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ከእስራኤል ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድን (ዶ.ር) ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል።
ውይይቱ የእስራኤል ባለሃብቶች በክልሉ ኢንቨስት በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው። የአማራ ክልል ሰፊ የኢንቨስትመንት አቅም ያለው ክልል ነው። በክልሉ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሃብቶች ኢንቨስት ያደርጋሉ።
የክልሉ መንግሥት ባለሃብቶች ወደ ክልሉ መጥተው መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈስሱ በተደጋጋሚ ጥሪ ያቀርባል። የእስራኤል ባለሃብቶችም ክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ ተጠቅመው ኢንቨስት ለማድረግ ነው ከርእሰ መሥተዳደሩ ጋር እየመከሩ የሚገኙት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!