
ደሴ: ታኅሣሥ 5/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ.ር) በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የልማት ቱሩፋት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በዞኑ በሚገኙ አካባቢዎች የበጋ መስኖ ስንዴን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በወረዳው በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ዜጎች የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ እያከናወኑ መኾኑን የቃሉ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሙሕዲን አሕመድ ተናግረዋል።
አርሶ አደሮች በሌማት ትሩፋት የተገኙ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ የኑሮ ውድነቱ እንዲረጋጋ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ያሉት ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን ናቸው።
በዞኑ አንፃራዊ ሰላም መኖሩ ለግብርና ሥራ እንቅስቃሴ ዓይነተኛ ሚናን እየተጫወተ መኾኑንም ገልጸዋል፡:
የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ.ር) በጉብኝታቸው የተመለከቷቸው የሌማት ትሩፋት ሥራዎች አበረታች መኾናቸውን እና የግብርና ሥራዎች በሜካናይዜሽን የተደገፉ መኾናቸው የተሻለ ምርት ለማምረት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
በጉብኝቱ የፌዴራል፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- ሰልሀዲን ሰይድ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!