
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 5/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዓባይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኀበር 14ኛውን መደበኛ የባለ አክሲዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል።
ጉባኤው የተካሄደው የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት የኩባንያው ማኔጅመንት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው።
ዓባይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር በበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ 801 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ማስመዝገቡን የቦርድ ሠብሣቢው አባተ ስጦታው ጠቅሰዋል።
ከባለፈው ዓመት 18 በመቶ ዕድገት ማሳየቱንም ገልጸዋል። ኩባንያው ባለፉት 10 ዓመታት 23 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡንም አቶ አባተ ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ የኩባንያው የሃብት መጠን 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 23 በመቶ ዕድገት በማሳየት 92 በመቶ ስኬታማ መኾኑንም አቶ አባተ ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!