የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት በትብብር እንዲሠራ ተጠየቀ።

26

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ዓለም አቀፍ የፀረ- ኤድስ ቀንን “ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይቪ አገልግሎት ለሁሉም” በሚል መሪ ሃሳብ በፓናል ውይይት አክብሯል።

የጤና ባለሙያዎቸ፣ ቫይረሱ በደማቸው የሚኖሩ ወገኖች ማኅበራት እና ልዩ ልዩ ባለድረሻ አካላት በውይይቱ ታድመዋል።

ስርጭቱን ለመግታት አስተማሪ የኾኑ የኪነጥበብ ሥራዎች እና የሻይ ቡና ምክክር መድረኮች በስፋት ሊሠራባቸው እንደሚገባ የውይይቱ ታዳሚዎች አሳስበዋል።

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ምክትል ኅላፊ ሲስተር ረቂቅ መንግሥቴ ስርጭቱን ለመግታት የጤና ባለሙያዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት እና ሚዲያዎች ቀድሞ በነበረው ትኩረት ልክ ኅብረተሰቡን የማስተማር ኅላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት።

የከተማ አሥተዳደሩ ጤና መምሪያ ኀላፊ ዘላለም ጌታቸው የውይይቱ ታዳሚዎች በሃሳብ፣ በኢኮኖሚ እና ግንዛቤ በመፍጠር ሊረዳዱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ ለማከናወን ዝግጅት ተደርጓል” ግብርና ቢሮ