“በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

35

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እየተገነቡ ካሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተጓዳኝ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አስታውቀዋል።

በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሸኽ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ድጋፍ የተገነባውን የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መርቀን ከፍተናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት።

ማዕከሉ ወላጅ የሌላቸውንና በችግር ውስጥ ያሉ ህጻናትን ከማሳደግ ባሻገር የሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ትብብር ማሳያ መኾኑንም ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአዲስ አበባ መንገዶች የነገውን ዕድገት ጭምር እንዲሸከሙ ተደርገው በጥራት እየተሠሩ ነው።
Next articleየኤች አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት በትብብር እንዲሠራ ተጠየቀ።