
ደሴ: ታኅሳስ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስተሩ አለሙ ስሜ (ዶ.ር) በደሴ ከተማ ውስጥ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል። ሚኒስትሩ ከደሴ ከተማ አሥተዳደር መሪዎች ጋር በመኾን ነው የኮሪደር ልማት ሥራዎች፣ መናኻሪያ፣ አስፋልት መንገድ፣ ድልድይ፣ የስማርት ሲቲ ትግበራ፣ የመሠረተ ልማቶች ዕድሳት፣ በከተማ ግብርና እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች እና ሌሎችንም የልማት ተግባራትን የተመለከቱት።
በደሴ ከተማ ውስጥ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ስም እና ታሪክ የሚመጥኑ እና ለሌሎች አካባቢዎችም ተምሳሌት እንደሚኾኑ ገልጸዋል። በተለይም ሕዝቡን እና መሪዎችን በማቀናጀት የተሠራው ሥራ አርዓያነት ያለው እንደኾነም ተናግረዋል። በቀጣይም አበረታች ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ቀን ከሌት በመሥራት በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ መኾናቸውን ተናግረዋል።
ደሴ ከተማ በከፍተኛ የለውጥ ጓዳና ላይ ናት ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የሚታዩ የልማት ተግባራትም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
ዘጋቢ:- ደምስ አረጋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!