ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የቃሊቲ ኢንዱስትሪ ዞን እና የልህቀት ማዕከልን ጎበኙ።

43

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የቃሊቲ ኢንዱስትሪ ዞን እና የልህቀት ማዕከልን ጎብኝተዋል። ጉብኝታቸውን አስመልክተውም የሚከተለውን መልእክት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ኮርፖሬሽኑ በተለያዩ ሀገራዊ ስትራቴጂክና ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽዖ ለማጠናከር የጀመረው ተቋማዊ ሪፎርም አበረታች ነው።

ከዚህም ባለፈ የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዞን በመገንባት በተኪ ምርትና በውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይ የጀመረው እንቅስቃሴ ለዘርፉ እመርታዊ ለውጥ ወሳኝ ነው።

የኢንዱስትሪ ዞኑ የማምረት ዐቅሙን በማሳደግ የግንባታ ግብአቶችን እያመረተ መሆኑ በዘርፉ የሚያጋጥም የግብአት እጥረትን በእጅጉ ይቀርፋል።

ኮርፖሬሽኑ የኢትዮጵያን የግንባታ ኢንዱስትሪ ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ተቋማዊና ሀገራዊ ሚናውን ማጠናከርና ዐቅሙን እንዲያጎለብት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሕዝቡን ጥያቄ እና ምሬት ሊፈታ የሚችል የፍትሕ ሥርዓት ለመዘርጋት በተግባር እየተሠራ ነው” የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ.ር)
Next articleየደሴ ከተማን ታሪክ የሚመጥኑ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾናቸውን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ.ር) ተናገሩ።