
ወልድያ፡ ታኅሣሥ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ሀራ ከተማ አሥተዳደር “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገን ሰብዕና ይገነባል” በሚል መሪ መልእክት በዓለም አቀፉ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው የጸረ ሙስና ቀን ተከብሯል።
የሰሜን ወሎ ዞን የሥነ ምግባር መኮንን ደሳለኝ ማዕረጉ ሥነ ምግባር የተላበሰ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ተደራሽ በማድረግ ብልሹ አሠራርን መታገል እንደሚገባ አሳስበዋል። ሙስናን በመታገል ረገድ የወጣቶች ድርሻ ከፍተኛ መኾኑንም አመላክተዋል። የሀራ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ሰኢድ የሙስና ወንጀልን መከላከል ለመንግሥት አካል ብቻ የሚተው አይደለም ነው ያሉት።
በጸረ ሙስና ትግል የተገኘው ውጤት ዘላቂ እንዲሆን የኅብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ተናግረዋል።
ሙስናን እና ብልሹ አሠራሮችን በመታገል የመንግሥትን እና የሕዝብን ሀብት መታደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!