ከትምህርት ገበታ ውጭ የኾኑ ሕጻናትን መመለስ እና ትውልድን ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።

40

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት ትውልድን በትምህርት የመታደግ የንቅናቄ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ፣ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢየሩስ መንግሥቱ፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ ርእሳነ መምህራን፣ መምህራን እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ ደስታ አስራቴ መምህርነት አንጋፋ ሙያ ነው፣ መምህር ደግሞ አንጋፋ ሙያተኛ ነው፣ መምህርነት ትውልዱን በዕውቀት የሚያንጽ የተከበረ ሙያ ነው ብለዋል።

በትምህርት ተቋሙ ላይ ሥብራት መደረሱንም አመላክተዋል። በርካታ ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መኾናቸውንም ተናግረዋል። ከትምህርት ገበታቸው የራቁ ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት ማምጣትና ትውልዱን የመካስ ዓላማ ያለው መድረክ መኾኑንም አንስተዋል። ከደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ተማሪዎችን ማብቃት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የተቋረጠውን ትምህርት ለማስጀመር፣ በትምህርት የከሰረውን ትውልድ ለመካስ፣ የትምህርት ዘርፉን ስብራት ለመመለስ የመምህራን ሚና የጎላ ነው ያሉት ኃላፊው የምንወያየው ትውልድን በማስቀጠልና ባለማስቀጠል መካከል ላይ ኾነን ነው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጤና ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ምርምር አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡
Next articleከ190 ሺህ ኩንታል በላይ ጥራቱን የጠበቀ ሰሊጥ ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን ምዕራብ ጎንደር ዞን አስታወቀ።