የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በባሕላዊ የእርቅ ሥርዓት ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው።

32

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በባሕላዊ የእርቅ ሥርዓት፣ በፍርድ ቤት መር አሠያሚነት እና በግልግል ዳኝነት ዙሪያ ያተኮረ የውይይት መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የፍትሕ ሚኒስትር ድኤታ ኤርምያስ የማነብርሃን (ዶ.ር) እንዲሁም ሌሎች የክልሉ መሪዎች፣ የተለያዩ ክልሎች የፍትሕ ተቋማት መሪዎች፣ ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች እየተሳተፉ ነው።

ለሦስት ቀናት በሚቆየው ውይይት ላይ የአማራ ክልል ግጭት መፍቻ ባሕላዊ የሽምግልና ሥርዓቶች በጥናት ይቀርባሉ። ማኅበረሰብን መሰረት ያደረገ ፍትሕ በኢትዮጵያ እና የፍትሕ ሚኒስቴር ያለው ሚና ምን እንደሚመስልም ይዳሰሳል።

ከሲዳማ እና ሌሎች ክልሎች የተጋበዙ የፍትሕ ተቋማትም የየአካባቢውን ባሕላዊ የግጭት መፍቻ የሽምግልና ሥርዓት ተሞክሮዎች ያቀርባሉ።

የአማራ ክልል ባሕላዊ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ መነሻ ረቂቅ አዋጅም ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።

zየአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተመድ የአንካራው ስምምነት በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት የሚያስችል መልካም እርምጃ መሆኑን ገለጸ።
Next article“ዜጎች በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ጠንካራ አመኔታ እንዲኖራቸው የሚያስችል የፍትሕ ሥርዓት ለመዘርጋት እንሠራለን” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ