ዘላቂ ሰላም ለመገንባት እና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሁሉም ድርሻ ወሳኝ ነው።

58

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር ደረጃ ዘላቂ ሰላም ለመገንባት እና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም የበኩሉን ሚና መወጣት እንደሚገባው የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ገልጸዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ አማካሪዎችና መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት በ2017 በጀት ዓመት አምስት ወራት በየዘርፉ የተከናወኑ ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማና የሥራ ትውውቅ ተካሂዷል።

በውይይቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት፣ የታዩ ውስንነቶችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ቀርበዋል።

የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ በተቋሙ ባለፉት አምስት ወራት በሰላም ግንባታ፣ በሀገር ግንባታ፣ በብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት፣ በፌዴራሊዝምና መንግሥታት ግንኙነት እንዲሁም በግጭት አስተዳደር የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል።

እንደ ሀገር የተመዘገበውን ውጤት ለማስቀጠል፣ ዘላቂ ሰላም ለመገንባትና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ሁሉም በየተሰማራበት መስክ መረባረብ እንደሚገባው አመልክተዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ከተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር እያከናወነ ያለውን ሥራ በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንዳለበት መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት እንደሚሠሩ የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አስታወቁ።
Next articleተመድ የአንካራው ስምምነት በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት የሚያስችል መልካም እርምጃ መሆኑን ገለጸ።