አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት እንደሚሠሩ የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አስታወቁ።

64

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የስልጣን ዘመናቸው ከመጠናቀቁ በፊት አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫዎች እንደሚኖሯት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

ስልጣናቸው በፈረንጆቹ 2026 ታሕሳስ የሚጠናቀቀው አንቶኒዮ ጉተሬስ በደቡብ አፍሪካ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ለማድረግ በቁርጠኝነት እሠራለሁ ብለዋል፡፡

ከአምስቱ ቋሚ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ጋር ሁለት ቋሚ የአፍሪካ አባላት እንዲኖሩ ስምምነት አለን ያሉ ሲሆን በዚህም አሳሳቢው ችግር መወገዱን አብስረዋል፡፡

55 ሀገራት ያሉት የአፍሪካ ህብረት በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ ውክልና እንዲኖረው በተለያዩ ጊዜያትና በተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በዚህም በፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ላይ ኮሚቴው በትኩረት እየሠራ እንደሆነ ጠቅሰው፥ አፍሪካ ቋሚ አባል ሳትሆን የዋና ፀሐፊነት ስልጣናቸውን እንደማያጠናቅቁ ያላቸውን ተስፋ መግለጻቸውን አርቲ ነው የዘገበው፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ቅንጅትና ትብብር ለጤናው ዘርፍ አስፈላጊ ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
Next articleዘላቂ ሰላም ለመገንባት እና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሁሉም ድርሻ ወሳኝ ነው።