ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ጋር በክልሉ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።

76

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና ከሌሎችም የሚኒስቴሩ ከፍተኛ መሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው። የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሥራ ኀላፊዎችም በውይይቱ ላይ እየተሳተፋ ነው።

በውይይቱ ወቅታዊ የወባ በሽታ ስርጭት እንዲገታ ብሎም ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ የሚሠሩ ሥራዎች ተነስተዋል። በክልሉ እየተካሄደ ያለው የኮሌራ በሽታ የክትባት ሂደትም የውይይቱ አካል ነው።

ክልሉ በጸጥታ ችግር ውስጥ የቆየ ከመኾኑ ጋር በተያያዘ በተለይም ለጤናው ዘርፍ እንቅፋት የኾኑ ጉዳዮች እንዲፈቱ በውይይቱ ተነስቷል።

መሪዎች በክልሉ የጤና ተደራሽነት እና ተያያዝ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እና የቀጣይ አቅጣጫዎችንም እንደሚያስቀምጡ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአካል ጉዳተኞች ራሳቸውን ችለው በመሥራት ከተረጅነት እንዲላቀቁ ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
Next article“ቅንጅትና ትብብር ለጤናው ዘርፍ አስፈላጊ ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)