የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የለውጥ ሥራዎችን ጎበኙ።

36

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በባሕር ዳር ከተማ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጀመራቸው ተቋማዊ የለውጥ ተግባራት ምቹ የሥራ ቦታ የመፍጠር እና የለውጥ ሥራዎች እንዲሁም የአካባቢዉን የኮሪደር ልማት ከቢሮው ጋር አያይዞ የማልማት ሥራ ለሌሎች ተቋማትም በአርያነት የሚወሰድ መሆኑን ጠቅሰዋል። የፍርድ ቤቱ ተቋም ግንባታ ላይ የተጀመረው ሥራ መጠናከር ለክልሉ ሕዝብና መንግሥት ከፍተኛ ትርጉም አለው ብለዋል።

በጉብኝቱ የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በባሕር ዳር ከተማ የጤና ተቋማትን እየጎበኙ ነው።
Next articleየፈተና ጥሪ ማስታወቂያ !