
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በባሕር ዳር ከተማ የጤና ተቋማትን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ፣ የጤና ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር ደረጀ ደጉማ፣ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር መልካሙ አብቴ፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ሚኒስትሯ የባሕር ዳር ጤና ጣቢያ እና የፈለገ ሕይዎት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ የጤና ተቋማቱ የተሻለ የሕዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚሠራ ተናግረዋል። ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የጤና ተቋማትን መጎብኘታቸው ተቋማቱ የተሻለ ሥራ እንዲሠሩ እና ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ያደርጋቸዋል ነው ያሉት። መሪዎቹ ተቋማት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!