የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ማነቆ እየፈታ ነው።

28

ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) እንደ ሀገር እየተተገበረ ያለው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲነቃቃ፣ የማምረት አቅሙ እንዲያድግ እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርቶች እንዲተኩ እያደረገ ነው። ይህ ንቅናቄ በአማራ ክልልም ለውጦችን እያመጣ ነው።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአሥር ዓመታት የሚተገበር መኾኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአማራ ክልል መጀመሩንም አስታውሰዋል። ሀገራዊ ንቅናቄው በአማራ ክልል እንዲጀመር የተደረገው ከሰሜኑ ጦርነት ማግስት ችግር የገጠመውን የክልሉን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት በመታሰቡ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ያለውን ማነቆ ለመፍታት ዓላማ አድርጎ እየሠራ መኾኑን ነው የተናገሩት። አምራች ኢንዱስትሪዎች የፋይናንስ፣ የኃይል አቅርቦት፣ የግብዓት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎች ማነቆዎች እንዳሉባቸውም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ዓላማም ማነቆዎችን መፍታት፣ የተቋማትን ቅንጅታዊ አሠራር ማስተካከል እና የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም የማሻሻል ሥራ እየሠራ መኾኑን ነው የተናገሩት። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በትኩረት እየተሠራበት መኾኑን ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ችግሮችን ለይቶ የመፍትሔ ሥራ እየሠራ መኾኑንም ተናግረዋል። ችግሮችን እየፈታ በመምጣቱ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም እንዲሻሻል አድርጓል ነው ያሉት። የማምረት አቅማቸውን የማሳደግ ሥራ አሁንም በትኩረት እየተሠራበት ነው ብለዋል።

የማምረት አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ነው ብለዋል። የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ ማነቆዎቻቸውንም መፍታት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ልማት እንዲገቡ ማድረግ ይገባልም ብለዋል።

ኢንዱስትሪዎች ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ተክተው እያመረቱ መኾናቸውንም አስታውቀዋል። ተኪ ምርቶችን የማምረት አቅም ዘንድሮ ከፍ እንደሚል ይጠበቃል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። ንቅናቄው ችግሮችን እየፈታ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ማስቀጠል ለክልሉ ፋይዳው ከፍ ያለ መኾኑንም አመላክተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleግብርና ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የጥጥ ማኅበር ጋር በጋራ ለመሥራት ተፈራረመ።
Next articleየጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በባሕር ዳር ከተማ የጤና ተቋማትን እየጎበኙ ነው።