ግብርና ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የጥጥ ማኅበር ጋር በጋራ ለመሥራት ተፈራረመ።

38

አዲስ አበባ: ታኅሳስ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ግብርና ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የጥጥ ማኅበር ጋር በጋራ ለመሥራት የፈጸመው ስምምነት ኢትዮጵያ ገበያውን በስፋት እንድትቀላቀል የሚያስችል ነው። ስምምነቱ አለምአቀፉን የጥጥ ምርት ገበያ ሰንሰለት በማሳለጥ በኩልም የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
የኢትዮጵያን የጥጥ ምርት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችል ቀጣናዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

ውይይቱ በዋናነት ሁሉን ያማከለ የጥጥ ምርትን ወደ ገበያ ማቅረብ ላይ ቀጣናዊ የልምድ ልውውጥ ማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል። ይህም የጥጥ ምርትን በማሳደግ ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪው ግብዓት ማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ካላት የጥጥ ምርት ሦስት በመቶውን ብቻ እንደምትጠቀም በመድረኩ ተነስቷል። ልክ እንደ ቡና ሁሉ ከፍተኛ የጥጥ ላኪ ሀገር ለመሆን ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባም ተገልጿል።

ከውይይት መድረኩ ጎን ለጎን የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ጥጥ እና ጨርቃጨርቅ ማኅበራት የአራትዮሽ የመግባቢያ ስምምነትም ተፈራርመዋል።

በመድረኩ ላይ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሐሰን ሙሐመድ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ተቋማት የተውጣጡ የዘርፉ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ የጤና ምርምር ጉባዔ እያካሄደ ነው።
Next articleየኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ማነቆ እየፈታ ነው።