
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አደራዳሪነት በአንካራ የተካሄደው የኢትዮጵያና የሶማሊያ ድርድር የጋራ አሸናፊነት የታየበት መሆኑ ሀገራችን ለጋራ ሰላምና ልማት ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ያስመሰከረ ነው ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፡፡
ሥምምነቱ ሀገራችን የባህር በር በሰላማዊ መንገድ ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ለቀጠናው ምጣኔ ሃብታዊና ማኅበራዊ ትስስር የጎላ ሚና እንደሚጫወት ያመላከተ ድርድርና ውይይት ነው፤ ይህ ሥምምነት ቀጠናዊ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ፣ የዕርስ በርስ ትብብርን፣ ምጣኔ ሃብታዊ ልማትንና ብልፅግናን የሚያረጋግጥልንም ይሆናል ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!