
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሚኒስትሯ ባሕር ዳር ደጅአዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ዶክተር መቅደስ ዳባ በባሕር ዳር በሚኖራቸው ቆይታ የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ የጤና ምርምር ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል።
ከጉባኤው ባለፈ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ የጤና ተቋማትን እንደሚጎበኙ እና ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጤና ዘርፍ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!