
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በአማራ፣ በትግራይ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን በአውሮፓ ሕብረት 2 ሚሊዮን ዩሮ የሚደገፍ የሰላም ግንባታ ፕሮጀክትን ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።
ፕሮጀክቱ ወጣቶች የሰላም ግንባታን ባሕል አድርገው እንዲሠሩ የማብቃትና የተሻለ የግጭት አፈታት አቅም እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑን ተገልጿል።
የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ.ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ሰላም የሁሉም ዜጋ ጉዳይ በመሆኑ ለዘላቂነቱ የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል።
መንግሥት በአንዳንድ የሀገሪቷ አካባቢዎች የተከሰቱ የሰላም እጦቶችን ለመቅረፍ በንግግር የመፍታት ቁርጠኛ አቋም በመያዝ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እየፈታ እንደሚገኝ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በመነጋገር ችግሮችን የመፍታት ነባር እሴቶችን በማጎልበት የሠላም እጦት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ሠላምን ለመገንባት እየሰራ ያለውን ሥራ አመስግነዋል።
ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት የሠላም ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ማረጋገጣቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!