
ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው። የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የልማት ሥራዎችን ለጎብኝዎች አሳይተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) እና ሌሎችም መሪዎች ተገኝተዋል።
የባሕር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት፣ ውቡ የጣና ማሪና መዝናኛ ቦታ፣ ሙሌ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ የዲፖ አረንጓዴ ልማት ሥራ እና የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎችንም መሪዎቹ ምልከታ ያደርጋሉ።
የምልከታው ዓላማ በግንባታ ላይ ያሉ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ተጠናቅቀው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውሉ እና ሥራ ላይ ያሉትም የበለጠ እንዲነቃቁ ለማስቻል ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!