በደብረ ማርቆስ ከተማ የተገኘዉን አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም ለኢንሸስትመንት ሥራው ምቹ ኹኔታ እየተፈጠረ ነው።

55

ደብረ ማርቆስ: ታኅሳስ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የተገኘዉን አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም ለአልሚ ባለሀብቶች ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳድር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታውቋል። በክልሉ የተከሰተው የሰላም እጦት አልሚ ባለሃብቶች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመፍታ ፈተና ኾኖ መቆየቱን መምሪያው ገልጿል።

የሰላም ችግሩ በኢንቨስትመንት ዘርፉ ላይ ተግዳሮት ኾኖ ቢቆይም በዚሁ ምክንያት የተቀዛቀዘዉን ኢንቨስትመንት ለማነቃቃት እየሠተራ መሆኑም ተገልጿል። የተገኘዉን አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም በከተማዋ አልሚ ባለሃብቶች በከተማ ግብርና በአምራች ዘርፍ እና በግንባታ አገልግሎት ዘርፍ ተሰማርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሠራ መኾኑን የመምሪያው ኃላፊ ተመስገን ተድላ ገልጸዋል።

ባለሃብቶች ለወጣቶች የሥራ እድል እንዲፈጥሩና ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ድጋፍ እየተደረገ ስለመኾኑም ተናግረዋል። በባለሃብቶች ዘንድ የሚነሱ ጥያቄችን ለመፍታት ከአጋር ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሠራርም ተዘርግቷል።

መምሪያ ኀላፊው ቀደም ሲል የገበያ ትስስር ችግር እንደነበር አንስተዋል። ችግሩን ለመፍታት ከሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራትና ከሌሎችም አጋር ተቀማት ጋር እየተሠራ መሆኑን ነዉ የገለጹት።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በከተማዋ 33 ባለሃብቶች በአዲስ ፈቃድ የወሰዱ ሲሆን 3 ባለሃብቶች ደግሞ ወደ ማምረት ገብተዋል። በዚህም ከ5 መቶ በላይ ወጣቶች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ከመምሪያ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዓለም አቀፉ የፀረ-ሙስና ቀን የማጠቃለያ መድረክ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
Next article“የጸረ-ሙስና ትግልን ውጤታማ አድርጎ የበለጸገች ሀገር ለመገንባት ሥነ ምግባር እና ሥርዓትን አስማማተው የያዙ ወጣቶችን ማሳተፍ ይገባል” ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ