
ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተገኙበት 21ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የማጠቃለያ መድረክ በአዲስ አበባ የአድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ የምክር ቤት አባላት፣ የፌደራል የስነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ.ር)፣ ሚኒስትሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
21ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል” በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!